- Home
- Apps
- Health & Fitness
- እርግዝናና ወሊድ Pregnancy Amharic
About Pregnancy እርግዝናና ወሊድ ሙሉ መረጃ
ይህ እርግዝና እና ወሊድ የተሰኘ የሞባይል አፕሊኬሽን ከቅድመ እርግዝና እስከ ድህረ ወሊድ ያለዉን እዉቀት አካቶ የያዘ ነዉ ፡፡በዚህ የሞባይል አፕሊኬሽን እርግዝናን በተመለከተ የሚደረግ ጥንቃቄና የእርግዝናን ሂደት በየሳምንት (እንደግመዋለን የየሳምንቱን የእርግዝና ሁኔታ) መረጃዎችን ያገኙበታል፡፡ እግርዝናዬ የሞባይል አፕሊኬሽን ለማንኛዉም ጥንዶች የሚሆንና ከማርገዝ በፊትም ሆነ ከእርግዝና ቡኋላ ሊከሰት የሚችልን አደገኛ ክስተቶችን ለመከላከልና ቀድሞዉ እንዲዘጋጁበት ይረዳቸዋል፡፡
አብዛኛዉ ጊዜ አዲስ ተጋቢዎች የመጀመሪያ እርግዝና ላይ ብዙ ያልጠበቁት ነገሮች ሲያጋጥማቸዉ በጣም ይደናገጣሉ፤ ስለዚህ ይህ አፕሊኬሽን ከዶክተር ክትትል ጋር ታጅቦ ብዙ ሊጠቀሙበት ያስችላቸዋል፡፡
አቶ ባል! ባለቤትዎ አርግዘዋል? እንኳን ደስ አልዎት! እንግዲያዉስ ለውድ ባለቤትዎ ሊያደርጉላት የሚችሉት ጥንቃቄዎችና በእርግዝና ጊዜ ሊታይባት የሚችሉትን ያልተለመዱ ባሕሪያትን በዚህ አፕሊኬሽን በመታገዝ ቀድሞ በማወቅ እንክብካቤና እርዳታ ሊያደርጉላት እንዲችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ስለሆነ በቀላሉ መንገድ ሞባይሎት ላይ ጭነዉ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡
በዚህ አፕሊኬሽን ያካተትናቸዉ ርዕሶች፡-
-የጽንስ አጀማመር፣ ለማርገዝ ወሳኝ ወቅት፣ የእርግዝና ግንኙነት፣ የወር አበባ መዘግየት እና መጥፋት፣ እርግዝናን ማረጋገጥ፣ የእርግዝና ምልክቶች፣ ማርገዝ አለመቻል (መካንነት)፣ የሴቶች መካንነት፣ የወንዶች መካንነት፣ በእርግዝና ወቅት ስለሚያጋጥሙ አደገኛ የጤና ምልክቶችና መፍትሔዎች፣ በቅድመ ወሊድ ስለሚሰጡ የሕክምና ትትሎች መረጃዎች፣ ወላጆች የቅድመ ወሊድ ክትትል በማድረግ የሚያገኙት ጥቅም፣ ጤናማ ፅንስና የተመጣጠነ ምግብ፣ እናትና ልጅ በእርግዝና ወቅት ፣ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ፣ ከ4ኛዉ -6ኛዉ ወራት ፣ ከ7ኛዉ -9ኛዉ ወራት ፣ እርግዝናና ኤች.አይ.ቪ. ፣ ከወሊድ በኋላ፣ ከወሊድ በኋላ ወሲብ፣ የአውሮፕላን በረራ፣ የተፈጥሮ ወሊድ እና የሲ-ሴክሽን (ቀዶ ጥገና) ወሊድ፣ ከወሊድ በኋላ ክብደትን መቀነስ፣ ህጻኑን መንከባከብ፣ እንቅልፍ ከወሊድ በኋላ .... የተሰኙትን ርዕሶች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን መረጃ ዘርዘር አድርጎ ይዟል፡፡
በእነዚህ መረጃዎች ላይ መቶ በመቶ ጥገኛ መሆንም የለብንም፡፡ እነዚህ መረጃዎች የሀኪምን ምክር እና የህክምና ባለሞያዎችን ምክር አይተኩም ወይም አማራጭ አይደሉም፡፡ መረጃዎቹ የተሟሉ ወይም ሙሉ በሙሉ መልስ የሚሰጡ ወይም አጠቃሎ የያዙ አይደሉም፡፡
እነዚህ መረጃዎችን ብቻ ተጠቅመን ምንም አይነት የህክምና እገዛ ወይም ምርመራ ማድረግ የለብንም፡፡ ከህክምና ጋር በተያያዘ ጥያቄ ካላችሁ ሀኪምን ማማከር ምንግዜም ቅድሚያ ሊሰጠዉ ይገባል፡፡ በአፕሊኬሽኑ ላይ ያለዉን መረጃ ብቻ በማንበብ የሀኪምን ምክር እና አስተያየት ማጣጣል የለብንም፡፡
አፕሊኬሽኑ ወደፊት ተጨማሪ መረጃዎችን አካቶ በየጊዜው ይሻሻላል፡፡ የተጠቃሚዎች አስተያየት እና ፍላጎትን ባማከለ መልኩ አፕሊኬሽኑን ለማሻሻል እንተጋለን፡፡ አስተያየት ካላቹ በኢ-ሜይል [email protected] ላኩልን፡፡ እባክዎን አስተያየታችሁ አይለየን።
ኦሮምኔት የሶፍትዌር እና የሞባይል አፕልኬሽን ዲቬሎፕመንት PLC ነቀምቴ ኢትዮጵያ
OROMNET Software and Application Development, Nekemte, Ethiopia
Pregnancy እርግዝናና ወሊድ ሙሉ መረጃ 4.71 Update
Requires Android: Android 5.0+
Architecture: arm64-v8a
Screen DPI: 160-640dpi
SHA1: 37ac5c47063e77fff3fcf76de8a56e69c180a8d7
Size: 26.27 MB
What's New:
Requires Android: Android 5.0+
Screen DPI: 120-640dpi
SHA1: 487a5888261ce370530bcb291a524a51eb41f1c4
Size: 13.13 MB
Requires Android: Android 5.0+
Screen DPI: 160-640dpi
SHA1: b725aacf917864dbd2bb782a9ddfe3d93d2feb49
Size: 12.5 MB
Requires Android: Android 5.0+
Screen DPI: 120-640dpi
SHA1: 986a2d7c885e10b0b6504000a940df2c683e8553
Size: 12.86 MB
Package Name:
Category:
Update Date:
2024-09-01
Latest Version:
4.71
Need Update:
Available on:
Requirements:
Android 5.0+
Report: